ሕብረተሰቡ ለኩላሊት ህሙማን ሕክምና ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሕብረተሰቡ ለኩላሊት ህሙማን ሕክምና ድጋፍ እንዲያደርግ የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ጥሪ አቀረበ፡፡
የበጎ አድራጎት ድርጅቱ የኩላሊት ህሙማን የኩላሊት ንቅለ ተከላ እስከሚያደርጉ ድረስ ለእጥበት (ዲያሊሲስ) የሚያስፈልጋቸውን ወጪ ለመሸፈን ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል፡፡
ህሙማኑ የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንዲያደርጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየተከናወኑ ቢሆንም ኩላሊት የሚለግሱ ሰዎች ባለመኖራቸው አብዛኛው ህመምተኛ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛል ነው ያለው፡፡
ድርጅቱ የሚያደርገው ድጋፍ የሕክምና አገልግሎቱ ከሚጠይቀው ከፍተኛ ወጪ አንጻር ለብዙ ህሙማን መድረስ እንዳልቻለ አጽንኦት ሰጥቷል፡፡
ስለሆነም ሕብረተሰቡ ለኩላሊት ህሙማን ሕክምና አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡