Fana: At a Speed of Life!

በባህር ዳር ከተማ ለኮሮና ቫይረስ መከላከል የተሰጠው ትኩረት አናሳ መሆን የቫይረሱ ስርጭት እንዲጨምር እያደረገው ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በባህርዳር ከተማ ለኮሮና ቫይረስ መከላከል የተሰጠው ትኩረት አናሳ መሆን የቫይረሱ ስርጭት እንዲጨምር እያደረገው መሆኑ ተገለፀ፡፡

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ አማረ አለሙ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቀመጡ ክልከላዎችን የማስተግበር እና እርምጃ የመውሰድ ስራ ተጀምሯል።

የቫይረሱን ስርጭት ለመግታትም በአዋጁ የተቀመጡ ክልከላዎችን ማስተግበር ቀዳሚ እና አማራጭ የሌለው ጉዳይ በመሆኑ እርምጃዎቹ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው የገለፁት።

በተለይም ችግሩ ጎልቶ በሚታይባቸው እና ህብረተሰቡ በብዛት በሚታይባቸው ቦታዎች ላይም በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል ምክትል ከንቲባው።

በአጠቃላይም በከተማዋም ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ትግበራ የተሰጠው ትኩረት አናሳ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

የመዘናጋቱ ውጤት ደግሞ በክልሉ ብሎም በባህር ዳር በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እንዲጨምር እያደረገው መሆኑም ነው የተነገረው፡፡

እንደ መጠጥ ቤቶች፣ ሆቴሎች፣ የግብይት ቦታዎች እና መሰል ሰዎች በብዛት የሚሰበሰቡባቸው ቦታዎችም ትኩረትን የሚሹ መሆናቸው ተገልጿል።

በአማራ ክልል እስከ ትናንትናው እለት ድረስ ብቻ 933 ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው የስንምት ሰዎች ህይዎት ደግሞ አልፏል፡፡

በዙፋን ካሳሁን

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.