የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባዉን አካሂዶ አራት የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
በዚህም መሰረት ፡-
1ኛ ራስን ችሎ የሚለማ ቦታ ዝቅተኛው ስፋትና የፊት ለፊት ገፅታ ርዝመት ( set back) አተገባበር ጥናት ላይ ተወያይቶ የከተማዋን እድገት ታሳቢ ያደረገ እና የአተገባበር ምቹነት ታሳቢ ባደረገ የቀረበዉ ጥናት ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
2ኛ በኮሪደር ልማት የለሙ ልዩ ልዩ መሰረተ ልማቶች እና የወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለስልጣን ለማቋቋም የቀረበዉ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ የማስተዳደር፣ አገልግሎት የመስጠት፣ የመጠበቅ፣ የማስተባበር እና የማቀናጀት ኃላፊነት እንዲኖረው ሆኖ እንዲቋቋም ወስኗል።
3ኛ የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ አስተዳደር አግባብነት ያለዉ አካል ሳይፈቅድ፤ የተያዙ ይዞታዎች አገልግሎት የመስጠት ጊዜን ለማራዘም በቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
4ኛ. ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች እና የኢንዱስትሪ ልማት ተቋማት ላይ ለመሳተፍ የቀረበ የመሬት ጥያቄ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!