ከ100 ኪሎ ግራም በላይ ካናቢስ ቤት ውስጥ ሸሽገው የተገኙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከ100 ኪሎ ግራም በላይ ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ ዕጽ በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሸሽገው የተገኙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
አደንዛዥ ዕጹ የአዲስ አበባ ፖሊስና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አጂብ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ መኖሪያ ቤት ላይ ባደረጉት ፍተሻ ነው የተያዘው ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ አደንዛዥ ዕጹን በከረጢት በመጠቅለል ወደ ገበያ ለማቅረብ ሲዘጋጁ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማዋ ፖሊስ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
በተጠርጣሪዎቹ ላይ ተጨማሪ ምርመራ የማስፋቱ ተግባር ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን÷ ተገቢውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማጠናከር ክስ እንደሚመሰረትባቸው ተመላክቷል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡