Fana: At a Speed of Life!

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ትስስርን በማጠናከር አብሮነትን ያሳድጋል – አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትን በማጠናከር መደጋገፍን አጉልቶ ያሳየ መልካም ተግባር ነው አሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በአፋር ክልል ሠመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎችን አከናውነዋል።

አቶ አወል አርባ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ አብሮነትን ከፍ በሚያደርጉ ተግባር ላይ ያደረጉት ድጋፍ አበረታች ነው፡፡

ተቋማቱ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውና እና የአቅመ ደካማ ቤቶችን ዕድሳት ሥራ ማከናወናቸው የሚመሰገን ተግባር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በክረምት ወራት አብረን የተከልናቸው ችግኞች በቀጣዩ ጊዜያት ለፍሬ በቅተው ምርታማነታቸውን የምንቋደስ ይሆናል ነው ያሉት።

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትን በማጠናከር መደጋገፍን አጉልቶ ያሳየ መልካም ተግባር መሆኑን አውስተዋል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ የመተሳሰብ እና የመረዳዳት በጎ ተግባራት እየተጠናከሩ መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን እየተባበርን መስራት ስንችል አቅማችን ይጨምራል ያሉት ሚኒስትሩ÷ መሠል ተግባራት መጠናከራቸው ድጋፍን በቀጣይ በራስ አቅም ለመሸፈን የሚደረገውን ጥረት እውን ማድረግ ያስችለል ብለዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.