Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ አጀንዳ ሆኖ እየተሰራበት ያለው ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀልን መከላከል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀልን መከላከል ብሔራዊ አጀንዳ ሆኖ እየተሰራበት ነው አሉ።

የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ጸረ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ቡድን 50ኛው የከፍተኛ ኃላፊዎች፣ 25ኛው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ እና ስምንተኛው የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የውይይት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀልን መከላከል ብሔራዊ ኮሚቴ ሊቀ መንበር የሆኑት ዓለምፀሐይ ጳውሎስ በጉባኤው ላይ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀልን ለመከላከል በትኩረት እየሰራች ነው።

ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍን ለመከላከል በቡድኑ ሀገራት መካከል ጠንካራ ትብብር ሊኖር ይገባል ብለዋል።

ጉባኤው በጋራ ከመምከር ባለፈ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን በመቆጣጠር የፋይናንስ ስርዓቱን ለማዘመንና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የጋራ ቁርጠኝነት መኖሩ የታየበት መሆኑን ገልጸዋል።

የቡድኑ አባል ሀገራት በችግሮች ላይ በመምከር የጋራ መፍትሄ ማበጀት እንዳለባቸው ጠቅሰው፤ በሀገራት መካከል ትብብር፣ ተጠያቂነትና የቴክኒክ ልህቀት ሊኖር ይገባል ነው ያሉት።

እነዚህን ችግሮች ለመከላከል የጋራ ተቋማትንና ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የከፍተኛ ኃላፊዎች ግብረ ኃይል ለምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ጸረ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ቡድን የጀርባ አጥንት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀልን ለመከላከል ትኩረት በመስጠት መንግስት 23 ተቋማትን የያዘ ብሔራዊ ኮሚቴ ማቋቋሙን ጠቁመው፤ ጉዳዩ ብሔራዊ አጀንዳ ሆኖ እየተሰራበት ነው ብለዋል።

በሀገራዊ ሪፎርሙ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀልን የመከላከል ሥራን ለማጎልበት ተቋማት እንዲጠናከሩ ተደርጓል ነው ያሉት።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.