Fana: At a Speed of Life!

ጤናማ የፋይናንስ ስርዓት ለመገንባት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ ይገባል – አቶ አህመድ ሺዴ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ ጤናማ የፋይናንስ ስርዓት ለመገንባት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ ይገባሉ አሉ የገንዘብ ሚኒስትር እና የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ጸረ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ቡድን ሚኒስትሮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አህመድ ሺዴ፡፡

የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ጸረ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ቡድን 50ኛው የከፍተኛ ባለሙያዎች፣ 25ኛው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ እና ስምንተኛው የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የውይይት ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

አቶ አህመድ ሺዴ በመድረኩ እንዳሉት፤ መድረኩ ለሁሉም አባል ሀገሮች የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ጸረ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ቡድን ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ማጭበርበርን እንዲሁም ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍን ለመከላከል ለሁሉም ኃላፊነት ይሰጣል።

ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍን መከላከል የቀጣናውን ደህንነት በማረጋገጥ አስተማማኝ ኢንቨስትመንት መሳብ እንደሚቻል ተናግረዋል።

የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ጸረ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ቡድን ማዕቀፍ ላይ ሀገራት ጥሩ እየሰሩ ቢሆንም ውስንነት እንዳለ ጠቁመዋል።

የህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍን ለመከላከል ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ የግሉንና የመንግስትን ትብብር በማሳደግ ቀጣናዊ አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ጸረ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ቡድን ራዕይ እንዲሳካ በጋራ የመስራትና የመተባበር ስራዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.