በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሳል አመራር ለውጤት የበቃው ህዳሴ ግድብ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሰጡት በሳል አመራር ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለውጤት እንዲበቃ አስችሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በቅርቡ ለተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ መቻልን ያሳየችበት፤ ስህተታችንን ያረምንበትም ጭምር ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳረጋገጡት፤ ግድቡ ክረምቱ ሲያልቅ ይመረቃል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የግድቡ ለውጤት መብቃት የአይቻልም ስሜትን የቀየረ የኢትዮጵያዊያንን የመልማት መሻት ጥያቄ የመለሰ ነው።
የግድቡ ግንባታ ፕሮጀክት የተጀመረው በኢህአዴግ ጊዜ እንደነበር አስታውሰው፤ ከመጀመር ባለፈ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ማስቀጠልና መፈጸም ሌላ ጉዳይ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ከለውጡ በፊት ፕሮጀክቱን በብቃት የመምራት ችግርና ሙስና እንደነበር አስታውሰው፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመራር ለችግሮች እልባት ሰጥቷል ብለዋል።
ግንባታው ከለውጡ በፊት በገጠመው ችግር ረጅም ጊዜ መውሰዱን ጠቅሰው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት አመራር ግድቡ ለውጤት እንዲበቃ አስችሏል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከለውጡ በኋላ ግድቡ በአግባቡ እንዲካሄድ የተሰጠው ትኩረት እና ክትትል የግድቡ ግንባታ ለውጤት እንዲበቃ ማድረጉንም አስረድተዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚመራው የለውጡ መንግስት ለሰጠው በሳል አመራር ሊመሰገን ይገባል ብለዋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ማንሰራራት የሚያበስር ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑ መገለጹ ይታወቃል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!