Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የጸጥታ አደረጃጀቶችን የማጠናከር ስራ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ሚሊሻ ጽህፈት ቤት በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የጸጥታ አደረጃጀቶችን የማጠናከር ስራ እየተሰራ ነው አለ።

የሚሊሻ እና የአድማ መከላከል አባላትን ሙያዊ አቅም የመገንባት ዓላማ ያለው ስልጠና በደብረ ብርሃን ከተማ እየተሰጠ ነው።

የክልሉ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስቻለ አላምሬ በስልጠና መድረኩ እንዳሉት፥ በክልሉ አጋጥሞ የነበረው የጸጥታ መደፍረስ በርካታ ኪሳራ አስከትሏል።

የጸጥታ ችግሩን ለመፍታት በተሰራው ስራ ውጤት መገኘቱን ገልጸው፤ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የጸጥታ አደረጃጀቶችን የማጠናከር ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በክልሉ እየተሰሩ ያሉ የልማት እና የሰላም ግንባታ ስራዎች ፍሬያማ እንዲሆኑ ትኩረት መደረጉንም ጠቁመዋል።

በጸጥታ ማስከበር ስራ ላይ ያለው የሰው ኃይል የጠንካራ ዲሲፕሊን ባለቤት እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ተናግረው፤ ይህም ለሰላም ማጽናት ስራው አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ስልጠናው የሰልጣኞችን ሞራልና ስነ ልቦና እንደሚገነባ ጠቅሰው፥ ሰልጣኞቹ በየደረጃው ያሉ አደረጃጀቶችንና ሕብረተሰቡን በማስተባበር ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ ይተጋሉ ነው ያሉት።

ሕብረተሰቡ የሰላሙ ዘብ በመሆን የበኩሉን ሚና እንዲወጣም አቶ አስቻለ ጥሪ አቅርበዋል።

ለአንድ ሳምንት በሚቆየው በዚህ ስልጠና ላይ የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የሚሊሻ፣ የፖሊስ፣ የክፍለ ጦር እና የሻለቃ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

በሰላም አሰፋ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.