Fana: At a Speed of Life!

በሱዳን በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ1 ሺህ ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሱዳን ዳርፉር ግዛት በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ ቢያንስ የ1 ሺህ ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
አደጋው የደረሰው በሀገሪቱ ያለውን ግጭት በመሸሽ በርካታ ተፈናቃዮች በተጠለሉበት ታራሲን መንደር መሆኑ ተገልጿል፡፡
ባሳለፍነው እሁድ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት የመኖሪያ መንደሩ መውደሙን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
አደጋው ከመከሰቱ አስቀድሞ በተከታታይ ቀናት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፥ በአካባቢው ለሚገኙ ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.