የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ስያሜዎች ይከበራሉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የ2017 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ስያሜዎች በመላው ሀገሪቱ ይከበራሉ አሉ፡፡
ሚኒስትሩ ባለፉት ዓመታት የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበሩ እንደነበር አስታውሰው፤ ዘንድሮም የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ስያሜዎች እና በልዩ ልዩ ዝግቶች በመላው ሀገሪቱ እንደሚከበሩ አብራርተዋል፡፡
ቀናቱ የዓመቱን ጉድለቶቻችን በመገምገም ለመጪው አዲስ ዓመት የምንሰራቸውን ስራዎች የምናቅድባቸው ናቸው ብለዋል፡፡
ባለፈው ዓመት የተገኘውን ህልም እና ትልም ለማህበረሰቡ በማስገንዘብ ለመጪው አዲስ ዓመት ግብዓት ለማድረግ በልዩ ስያሜ ቀናቶቹ እንደሚከበሩ ገልጸዋል፡፡
የ2017 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት የተለያዩ ስያሜዎች እና መሪ ቃል እንደተሰጣቸው ጠቅሰው፤ በዚህም ጳጉሜን 1 የፅናት ቀን የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ‘ፅኑ መሰረት ብርቱ ሀገር’ በሚል መሪ ቃል ይከበራል ብለዋል፡፡
ጳጉሜን 2 የህብር ቀን በሚል ስያሜ የሚከበር ሲሆን ‘ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ’ በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ይውላል ነው ያሉት፡፡
ጳጉሜን 3 የእምርታ ቀን የሚል ስያሜ የያዘ ሲሆን ‘እምርታ ለዘላቂ ከፍታ’ በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ገልጸዋል፡፡
ጳጉሜን 4 የማንሰራራት ቀን በሚል ስያሜ የሚከበር ሲሆን ‘ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት’ በሚል መሪ ቃል ይከበራል ብለዋል፡፡
ጳጉሜን 5 የነገው ቀን የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ‘ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ’ በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር አብራርተዋል፡፡
የዘንድሮ የጳጉሜን ቀናት በመላው ሀገሪቱ በተለያዩ ስያሜዎች ስናከብር ስኬቶቻችንን በማጉላት ድክመቶቻችንን ለማረም በመዘጋጀት የመሻገሪያ መንገዶችን በመተለም ነው ብለዋል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!