2017 ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት ዓመት ነው – ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እየተጠናቀቀ ያለው 2017 ኢትዮጵያን ከተረጅነት የሚያላቅቅ መሰረት የተጣለበት ዓመት ነው አሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፡፡
ሚኒስትሩ የ2017 በጀት ዓመት አበይት የመንግስት ክንውኖችን እንዲሁም የሚቀጥለው ዓመት ተስፋዎችን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ በለውጡ ዓመታት መንግስት በጠንካራ የልማት አካሄድ እና አካታች ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በርካታ ድሎችን አስመዝግቧል ብለዋል።
በዘላቂ ሀገር በቀል ሪፎርም በመመራት፣ ምርታማነትን በማሳደግ እንዲሁም የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ረገድ ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝገበዋል ነው ያሉት።
በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በርካታ የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት እና የወጪ ንግድን ማሳደግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረግ የግሉን ዘርፍ በኢኮኖሚው ተሳታፊ በማድረግ፣ በአረንጓዴ ዐሻራ እና የአየር ንብረት ለውጥ ስኬታማ ስራዎች መፈጸማቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በተባበሩት መንግስታት በፀጥታው ምክር ቤት ይቀርቡ የነበሩ ጫናዎችን መመከት መቻሉን አስታውሰው፤ ግድቡ እንዳይጠናቀቅ የተደረጉ ሙከራዎች መክሸፋቸውን አብራርተዋል፡፡
በአመራር ጥበብ እና ብልሃት እንዲሁም በህዝቡ የተደራጀ አቅም ግድቡ በማጠናቀቅ ታሪክ መስራት መቻሉንም ነው የገለጹት፡፡
በአጠቃላይ የተጠናቀቀው ዓመት የማንሰራራት ጅማሮ የታየበት ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ዓመቱ ኢትዮጵያ ውስብስብ ችግሮችን በማለፍ በሁሉም ዘርፍ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት ዓመት ነው ብለዋል፡፡
በሚኪያስ አየለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!