Fana: At a Speed of Life!

ታሪካዊ ከፍታ ላይ የሚገኘው የሩሲያ እና ቻይና ግንኙነት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው ከቻይና ጋር ያላት ሁሉን አቀፍ ግንኙነት ታሪካዊ ከፍታ ላይ እንደሚገኝ ተናገሩ።

የሩሲያ እና ቻይናን ትብብር ለማጠናከር ያለመ የዓለም አስተዳደር ኢኒሼቲቭ መድረክ ተካሂዷል።

በዚህ ከሻንጋይ ትብብር ፎረም ማግስት በቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ዛሬ ይፋ በሆነው በዚህ መድረክ የተሳተፉት ፕሬዚዳንት ፑቲን፤ ሀገራቸው ከቻይና ጋር ወዳጅ መሆኗን ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግን “የረጅም ጊዜ ጓደኛየ’ ሲሉ ስላላቸው ወዳጅነት ገልጸዋል።

የቻይና እና ሩሲያ ግንኙነት በዓለም አቀፍ ጫናዎች ሳይበገር በታሪካዊ ከፍታ ላይ ይገኛል ያሉት ፕሬዚዳንት ፑቲን÷ የሀገራቱ ግንኙነት በዲፕሎማሲያው ዓለም የጠንካራ ግንኙነት ምሳሌ መሆን ይችላል ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በበኩላቸው÷ ሁለቱ ሀገራት ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የተፈጠረውን የባለ ብዙ ዋልታ የዓለም አስተዳደር ስርዓትን ለማስጠበቅ በትብብር እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ከሩሲያ ጋር ትናንት አብረን ነበርን፣ ዛሬም አብረን ነን፣ ትብብራችን ለወደፊትም ይቀጥላል ነው ያሉት።

የሀገራቱ ግንኙነት ከሩሲያ ዩክሬኑ ጦርነት በኋላ የበለጠ እየተጠናከረ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን፤ በሁለትዮሽ ትብብሮች እንዲሁም በደቡብ ለደቡብ ትብብር እና ብሪክስ ማዕቀፎች በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ገለልተኛ የሆነችው ቻይና ከሩሲያ ጋር ያላት የንግድ ልውውጥ 240 ቢሊየን እንደሚደርስ ቢቢሲ እና አናዶሉ ዘግበዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.