Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ መቀመጫቸውን ያደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት የከተማ አስተዳደሩ እያከናወናቸው ለሚገኙ ተግባራት ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የአለም አቀፍ ተቋማት እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር ተወያይተዋል።
 
በቆይታቸው ምክትል ከንቲባው በዋናነት የተማሪዎች ምገባ ፣ የሸክላ እና የዕደጥበብ ማዕከላት ስራዎችን ጨምሮ ሌሎች በከተማዋ ውስጥ እየተሰሩ በሚገኙ ማህበራዊ ስራዎች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
 
የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ የዕደ ጥበብ እና የሸክላ ስራዎች ወደ ውጪ ገበያ እንዲቀርቡ የገበያ ትስስር እንዲፈጠር ትብብር እንዲያደርጉ እና በዘርፉ የተሰማሩ ነዋሪዎችን እንዲደግፉ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላቱም የከተማ አስተዳደሩ እያከናወናቸው ያሉ ስራዎች አድናቆት እንዳላቸው እና ድጋፍ እንደሚያደርጉም መግለፃቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
ኢንጅነር ታከለ ኡማ በእንሥራ የሸክላ ማዕከል የተዘጋጁ የሸክላ ውጤቶችን ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ በስጦታ አበርክተዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.