Fana: At a Speed of Life!

ኤሮ ዓባይ የድሮን ማምረቻ ለኢትዮጵያ ወታደራዊ አቅም …

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኤሮ ዓባይ የድሮን ማምረቻ የኢትዮጵያን ወታደራዊ አቅም አንድ ርምጃ ከፍ ያደርጋል፡፡

በቅርቡ በተካሄዱ እና እየተካሄዱ ባሉ የዓለም ጦርነቶች ከእግረኛ እና የምድር ላይ ውጊያ ይልቅ አብዛኛዎቹ በአየር ላይ እና በሳይበር የሚደረጉ ጦርነቶች ናቸው፡፡

የአየር ላይ ውጊያን የበላይነት ለመውሰድ ሀገራት ከሚታጠቋቸው ዘመናዊ የጦር ጄቶች በተጨማሪ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) በስፋት ጥቅም ላይ ሲያውሉ ይስተዋላል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኤሮ ዓባይ የድሮን ማምረቻን የሥራ እንቅስቃሴ በትናንትናው ዕለት በጎበኙበት ወቅት፤ አጥፍተው የሚጠፉ ድሮኖችን በስፋት እያመረትን እንገኛለን ብለዋል።

የኢትዮጵያ እዚህ አቅም መድረስ የሚኖረውን ፋይዳ በተመለከተ ፋና ዲጂታል ያነጋገራቸው በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ተመራማሪ አዲስ አለማየሁ÷ ኢትዮጵያ ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ ባለቤት መሆኗ በራስ መተማመኗን ያሳድጋል ብለዋል።

ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ለማዘመን የሚከናወኑ ተግባራት ተጠብቆ የቆየውን የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የሚያስቀጥል ነው።

በሰራዊቱ የባህር ሀይል እንደ አዲስ መቋቋሙን በአብነት አንስተው፤ ሰራዊቱን በቴክኖሎጂ የተሟላ እንዲሆን የሚደረገውን እንቅስቃሴ አድንቀዋል።

ሰራዊቱ ዘመኑ ባመጣቸውን ቴክኖሎጂዎች እና መሳሪያዎች ራሱን እያበቃ እና ለተልዕኮ ዝግጁ እየሆነ መምጣቱን ገልፀው፤ ኤሮ ዓባይ የድሮን ማምረቻ ፋብሪካ ሰራዊቱን በትጥቅ የማዘመን አንድ አካል ነው ብለዋል።

ፋብሪካው የኢትዮጵያን አየር ሀይል ክፍል እንዲሁም የሰራዊቱን የስለላ አቅም በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያጠናክረው ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ያላትን ወታደራዊ አቅም ተወዳዳሪነት ከፍ ያደርጋል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ ድሮን ማምረት መጀመሯ መንግስት ለፈጣን የቴክኖሎጂ ሽግግር የሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.