Fana: At a Speed of Life!

ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት መጎልበት ሚናውን እየተወጣ የሚገኘው የጋራ ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ ምክር ቤቱ የዴሞክራሲ ባህልን ለመገንባትና ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት መጎልበት የበኩሉን እየተወጣ ነው አሉ።

የጋራ ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው ጠቅላላ ጉባኤ የ2017 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ግምገማ፣ የ2018 ዕቅድ እና የአቅም ግንባታ ስልጠና ያከናውናል።

በጠቅላላ ጉባኤው ላይ አቶ ሰለሞን አየለ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ ለምርቃት ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት ጉባኤው መካሄዱ ልዩ ያደርገዋል፡፡

በሀገሪቱ ጠንካራ፣ ዘላቂ ልማት፣ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባት እና ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለህዝቦች አብሮነት፣ መቻቻል እንዲሁም ለሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና ጉልህ እንደሆነ ማመልከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የጋራ ምክር ቤቱ ድምጽ የሚሰማባቸውን መድረኮችን በመፍጠር ብሎም በሀገሪቷ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት እንዲፋጠን በርካታ ስራዎችን ሰርቷል ነው ያሉት።

መልካም አስተዳደር እንዲጎለብት ከማድረግ አኳያም ፓርቲዎች በጋራ እየሰሩ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ምርጫዎች ይበልጥ አሳታፊ፣ አካታችና ነጻ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታዎችን በጋራ የመፍጠር ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

ፓርቲዎች በተናጠል ያላቸውን የፖለቲካ ፍላጎት እውን ከማድረግ ጎን ለጎን በትብብር የመሥራት መልካም ጅማሮዎች እንዳሉ አንስተው፤ 11 የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት መፍጠራቸውን በአብነት ጠቅሰዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.