Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን ተግባራዊ በማድረግ ለዓለም የሚተርፍ አማራጭ መፍጠር ትችላለች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) አፍሪካ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን ተግባራዊ በማድረግ ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለዓለም የሚተርፍ አማራጭ መፍጠር ትችላለች አሉ፡፡

ሁለተኛው የዓለም ዓቀፉ የአፍሪካ የአየር ንብረት ሳምንት የሚኒስትሮች ውይይት በአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ ነው።

ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በካርቦን ልቀት ያላት አስተዋጽኦ አነስተኛ ቢሆንም በአየር ንብረት ተጽዕኖ በከፍተኛ ደረጃ እየተጎዳች ነው፡፡

የአየር ንብረት ቀውስ በአፍሪካ የልማት፣ የስራ እድል ፈጠራ እና የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲሁም በዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ፈተና እየሆነ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ሰለባ ብትሆንም ተጽዕኖውን ለመከላከል ጉልህ ሚና እየተጫወተች እንደምትገኝ አንስተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት እየተከናወነ የሚገኘው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመከላከል በተግባር ያሳየችው የሚያኮራ ርምጃ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በርካታ ተግባራትን ማከናወኗን ጠቅሰው፤ አሁንም ችግሩ አሳሳቢ በመሆኑ ጉዳዩ በልዩ ትኩረት መታየት ይገባዋል ነው ያሉት።

ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ አንድነታችንን ለማረጋገጥ፣ የጋራ ድምፃችንን ከፍ አድርገን ለማሰማት እና የአፍሪካን መብት የሚያስከብር ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት አጀንዳ ለመቅረጽ ታሪካዊ ዕድል ነው ብለዋል፡፡

አፍሪካ በዓለም ዓቀፍ የአየር ንብረት ድርድር ላይ የሚገባትን ቦታ እንድታገኝም በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.