Fana: At a Speed of Life!

የኅብር ቀን ሰላም፣ አንድነትና አብሮነትን ለማጠናከር የላቀ ፋይዳ አለው – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኅብር ቀን ዘላቂ ልማት፣ ሰላም፣ አንድነትና አብሮነትን አጠናክሮ ለማስቀጠል የላቀ ፋይዳ ይኖረዋል አሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ።

የኅብር ቀን “ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ዕለቱን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፥ የኅብር ቀን የተለያየ ባህል፣ ቋንቋ፣ ማንነትና እሴት ያለን ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የብዝሃነታችንን ጌጥና ውበት የምናከብርበት ነው ብለዋል።

ሀገራዊ እና ክልላዊ እሴቶች፣ ባህሎችና ወጎች ህብረ ብሄራዊ አንድነት እና ብዝሃነትን የሚያጠናክሩ ውድ ሀብቶቻችንን ያጎላል ነው ያሉት።

የሐረሪ ክልል የተገነባበትና የሚታወቅበት የተለያየ ማንነት፣ ቋንቋና ሃይማኖት ያላቸው ህዝቦች በሰላም፣ በመቻቻል፣ በአብሮነትና በወንድማማችነት የመኖራቸው እውነታ በብዝሃነት ላይ የተመሰረተ ኅብር እጅግ ጠቃሚ ሀብት ለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

የክልሉ ህዝብ በተለያዩ መድረኮች፣ በስራ ቦታዎችና በመኖሪያ አካባቢው ሁሉ ዕለቱን እንደ አንድ ቤተሰብ ተሰባስቦ ብዝሃነቱን፣ ማህበራዊ ትስስሩን፣ መቻቻልና የወል እሴቶቹን በሚያጠናክር አግባብ እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.