ብዝኃነት አብሮነትን የሚያጠናክር የአሸናፊነት ኃይል ነው – አቶ መሐመድ እድሪስ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብዝኃነት አብሮነትን የሚያጠናክር መልካም ዕድልና በመተማመን ለመኖር የሚያስችል የአሸናፊነት ኃይል ነው አሉ የሰላም ሚኒስትር ሐመድ እድሪስ።
“ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን የኅብር ቀን በማስመልከት የፓናል ውይይት ተካሂዷል።
ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ኢትዮጵያውያን ጥንታዊና ገናና ታሪክ ያላት ሀገራችን የገነባቻቸውን ገንቢ እሴቶች በመጠበቅ የብሔር፣ የኃይማኖት፣ የቋንቋ፣ የባህል ልዩነቶች ሳይገድቧቸው በየዘመናቱ የተፈጠሩ ችግሮችን በመቋቋም ድሎችን ተጎናጽፈዋል።
የጋራ አኩሪ ታሪክ፣ የጋራ ሀብቶቻችን፣ የጋራ ማህበራዊ እሴቶቻችንን፣ በደም የተሳሰረ፣ በኢትዮጵያዊነት የተጋመደ የጋራ ሀገራዊ ማንነትና በጋራ የመበልፀግ ዕድላችንን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድል በማደስ ወደፊት መስፈንጠር ይኖርብናል ብለዋል።
የፍትህ ሚኒስትር ሀና አርአያሥላሴ በፓናሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ሁለንተናዊ ሀገራዊ ስኬቶችን ለማስቀጠልና ተግዳሮቶችን ለመሻገር ሀገራዊ ትርክትን ማስረጽና አብሮነታችንን ማጠናከር አለብን ነው ያሉት፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ በዓለም ቅርስነት ያስመዘገበቻቸው ሀብቶቻችን የአብሮነት ውጤት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የሰላም፣ የፍትህ እና የትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በጋራ ባዘጋጁት የፓናል ውይይት ላይ ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!