የኅብር ቀን በሲዳማ ክልል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኅብር ቀን “ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ ቃል በሲዳማ ክልል በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል፡፡
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ በየነ ባራሳ በመርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢትዮጵያ በብዝሀ ማንነቶች የጠነከረች የሁላችንም ቤት ናት ብለዋል፡፡
የኅብር ቀን በአንድነትና በራስ አቅም ገንብተን የጨረስነውን ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለማስመረቅ በተጋጀንበት ወቅት የሚከበር መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው አመልክተዋል፡፡
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው፥ ውበትና ጸጋችን የሆነው ኅብራዊነት ጎልብቶ ታሪክ እንድንሰራ አስችሎናል ብለዋል።
በክልሉ በሁሉም መስኮች ድል ማስመዝገብ እንደተቻለ ገልጸው፥ ብሄር ብሄረሰቦች ያለምንም ችግር እሴቶቻቸውን እያጎለበቱ በክብርና በአንድነት የሚኖሩበት የብዝሃነት መገለጫ ክልል መፍጠር መቻሉን ጠቁመዋል።
በኅብር ቀን አከባበር መርሐ ግብር ላይ የክልሉ ሴክተር ቢሮዎች ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ያዘጋጇቸው ልዩ ልዩ ሁነቶች ተካሂደዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!