ጉባኤው ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ የሆኑ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ያደርጋል – ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 2ኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ የሆኑ አጀንዳዎችን በጋራ ማስቀመጥ ላይ ትኩረት ያደርጋል አሉ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)።
ሚኒስትሯ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚካሄደውን 2ኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
ጉባኤው በሁለት አጀንዳዎች ላይ መሰረት አድርጎ እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን፥ በቅድሚያ የአፍሪካን የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት መሰረት ያደረጉ አህጉራዊ መፍትሄዎች ዕውቅና እንደሚሰጣቸው አንስተዋል።
ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ፋይናንስም በጉባኤው ተከታዩ አጀንዳ እንደሚሆን ነው ሚኒስትሯ በመግለጫቸው የጠቆሙት።
ለዚህ ግብዓት የሚሰበሰብበት ቅድመ ጉባኤም ከነሀሴ 28 ጀምሮ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በመሪዎች ጉባዔ የሚጠበቀው የአዲስ አበባ ዲክላሬሽን ዋና ዋና የትኩረት አጀንዳዎችን በማደራጀት ለብራዚሉ ኮፕ 30 የማዘጋጀት ስራ እንደሚከናወን ተመላክቷል።
ይህም የአፍሪካን ድምፅ አንድ ለማድረግ ያለመ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፥ ለዚህ የሚሆኑና አፍሪካን ይጠቅማሉ የተባለላቸው ከ130 በላይ ኢኒሼቲቮች ከተለያዩ ሀገራት ተሰብስበዋል።
በጉባኤው ላይ 25 ሺህ ያህል ተሳታፊዎች እንደሚገኙና ከጉባዔው ጎን ለጎን 199 የሚሆኑ ውይይቶች እንደሚደረጉ ይጠበቃል።
43 የሚሆኑ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ አልሚዎች በኤግዚቢሽን ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ በመግለጫው ተነስቷል።
በአሸናፊ ሽብሩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!