ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የአፍሪካ እና ካሪቢያን ሀገራት ትብብር እንዲጠናከር ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአፍሪካ እና ካሪቢያን ሀገራት አንድነትና ትብብር እንዲጠናከር ጥሪ አቀረቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 2ኛው የአፍሪካ-ካሪቢያን ማህበረሰብ ጉባኤ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የአፍሪካ እና ካሪቢያንን አጋርነት ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የአፍሪካ-ካሪቢያን ማህበረሰብ አጋርነት ሁለቱ ወገኖች ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶችን ለመጋፈጥ በጋራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አመላካች መሆኑን ጠቁመዋል።
ዓለም እየተቀየረ በመሆኑ በአንድ ወቅት ችላ የተባሉ ድምጾች ሊሰሙ ግድ የሚልበት ወቅት ላይ ነን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በዚህ አዲስ ምዕራፍ በተናጥል ሳይሆን አንድ ሆነን መናገር አለብን ብለዋል።
የአፍሪካ እና ካሪቢያን ሀገራት ትብብር በእድል ላይ የተመሰረተና አሁናዊ እውነታዎችን በሚያንጸባርቁ ማዕቀፎች የሚመራ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል፡፡
ሀገራት ብቻቸውን መንቀሳቀስ በማይችሉበት ሁኔታ ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶችን ለመቋቋም ቀጣናዊ አንድነት ወሳኝ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!