የሻደይ፣ አሸንድየ፣ ሶለልና እንግጫ ነቀላ በዓላት የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ ሲከበሩ የቆዩት የቡሔ፣ የሻደይ፣ አሸንድየ፣ ሶለል እና እንግጫ ነቀላ በዓላት የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲ በመርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት፥ የብሔር ብሔረሰቦች መገለጫ የሆኑ ባህሎች ሳይበረዙ ለትውልድ እንዲተላለፉና ኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነትን የሚያስቀጥሉ እንዲሆኑ በትኩረት ይሰራል።
የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ በዓላቱ በየአካባቢው ብቻ ተወስነው መቆየታቸውን አስታውሰው፥ የሀገር አቀፍና የዓለም አቀፍ እውቅና ባለቤት ለማድረግ በዚህ መንገድ መከበሩ ፋይዳው ትልቅ ነው ብለዋል።
የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ መልካሙ ጸጋዬ እንዳሉት፥ በዓላቱ ትውፊታቸውን ጠብቀው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባለው መንገድ እንዲያድጉና ዓለም አቀፍ በዓላት ሁነው እንዲከበሩ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ሕዝብ በአንድነትና በኅብረት የሚያከብራቸው በመሆኑ ለሰላም ያላቸው ፋይዳ ከፍ ያለ እንደሆነ ጠቅሰው፥ ማኅበረሰቡ በዓላቱን በመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
በደሳለኝ ቢራራ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!