በክልሉ ለ745 ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በክልሉ የሕግ ፍርዳቸውን ሲፈጽሙ የቆዩ 745 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወስኗል።
ውሳኔው የክልሉ የይቅርታ ቦርድ፣ ታራሚዎቹ ካቀረቡት የይቅርታ ጥያቄ በመነሳት በይቅርታ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያዎች መሰረት መስፈርቱን የሚያሟሉትን በጥልቀት መርምሮ ለክልሉ መንግስት ካቀረበ በኋላ የተላለፈ መሆኑ ተጠቁሟል።
የይቅርታ ቦርዱ በምርመራው ወቅት የመንግሥትን፣ የህዝብንና የታራሚዎችን ጥቅም ባገናዘበ መልኩ ግምገማ አድርጎ ለ720 ወንድ እና 25 ሴት ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጓል።
የይቅርታ ተጠቃሚ የሆኑት ግለሰቦች በማረሚያ ተቋም በነበራቸው ቆይታ በመልካም ሥነ ምግባራቸው መታረማቸውንና መታነፃቸውን የሚያረጋግጥ በቂ መረጃ የቀረበላቸው መሆኑም ተረጋግጧል።
የክልሉ መንግስት በይቅርታ ከእስር የሚለቀቁ ታራሚዎች ከዚህ በኋላ ለህብረተሰቡ የስጋት ምንጭ ሳይሆኑ ሰላምን የሚሰብኩ፣ አምራችና ህግ አክባሪ ዜጎች በመሆን ማህበረሰቡን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ማቅረቡን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!