2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2017 (ኤፍ ኤምሲ) ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
ጉባኤው ‘ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን ማሳለጥ፣ የአፍሪካን አረንጓዴ ልማት በፋይናንስ መደገፍ’ በሚል መሪ ሀሳብ ነው ከጳጉሜን 3 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄደው።
በጉባዔው መክፈቻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የአንጎላው ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ጆኣኦ ሎሬንቾ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ እና ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች፣ እንዲሁም ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የመጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
ጉባዔው ማህበረሰብ ተኮር መፍትሄዎች ጎልተው የሚንፀባረቁበት፣ የአፍሪካ የጋራ አጀንዳ የሚቀረጽበት፣ እንዲሁም ሀገራት ለአየር ንብረት የገንዘብ ድጋፍ፣ የማጣጣሚያ እቅድ እና ዘላቂ ዕድገት ቃል ኪዳን የሚገባበት ይሆናል ነው የተባለው።
በመድረኩ አካባቢያዊ መፍትሄዎችን ከአህጉራዊ የአየር ንብረት ስትራቴጂዎች ጋር ማስተሳሰር በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ምክክር ይደረጋል ተብሏል።
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ሳምንት መድረኮች እና የአፍሪካ-ካሪቢያን የጋራ ጉባኤ በደማቅ ሁኔታ በአዲስ አበባ ሲካሄዱ መቆየታቸው ይታወሳል።
በመሳፍንት ብርሌ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!