የ2ኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ሀገራት ጉባዔ ተሳታፊዎች ለስራ ጉብኝት ሻሸመኔ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 2ኛዉ የአፍሪካ ካሪቢያን ሀገራት ጉባዔ ተሳታፊዎች ለስራ ጉብኝት ሻሸመኔ ከተማ ገብተዋል፡፡
ተሳታፊዎቹ ሀዋሳ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገዉላቸዋል።
የካሪቢያኗ ሀገር የሆኑ ጃማይካ ዜጎች በሻሸመኔ ከተማ እንደሚኖሩ ይታወቃል።
ጃማይካዎችን ለማግኘት የካሪቢያን ሰዎችን ጨምሮ ሌሎች የካሪቢያን ሀገራት ዜጎች ሻሸመኔ ከተማ እንደሚመጡ ነው የተገለጸው፡፡
በ2ኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ሀገራት መሪዎች ጉባዔ ተሳታፊዎች የካሪቢያን አፍሪካ ሀገራት ግንኙነት ምሳሌን ለመጎብኘት ነዉ ሻሸመኔ ከተማ የገቡት፡፡
2ኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ሀገራት መሪዎች ጉባዔ “ለአፍሪካውያንና ዘርዓ አፍሪካውያን የማካካሻ ፍትሕን ለመሻት አህጉር ተሻጋሪ አጋርነት” በሚል መሪ ሀሳብ ትናንት በአዲስ አበባ ከተማ መካሄዱ ይታወቃል።
በጌታቸዉ ሙለታ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!