በየዘርፋ የተመዘገበው ለውጥ ኢትዮጵያ በቀጣይ የምትደርስበትን ከፍታ የሚያመላክት ነው
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ በየዘርፋ የተመዘገበው ለውጥ ኢትዮጵያ በቀጣይ የምትደርስበትን ከፍታ የሚያመላክት ነው አሉ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ፡፡
ጳጉሜን 3 የእመርታ ቀን በሳይንስ ሙዚየም “እመርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡
ቀኑ በሀገሪቱ ባለፉት ሰባት ዓመታት የተመዘገቡ ሁለንተናዊ ስኬቶች እና ድሎች የሚቃኙበት ነው።
ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት ተግባራዊ የሆኑ የለውጥ ስራዎች አስተማማኝና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚን ለመገንባት አስችለዋል፡፡
በዚህም ቁልፍ የልማት ዘርፎች በሆኑት በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በገቢ አሰባሰብና በሌሎች ዘርፎች ተጨባጭ እድገት እየተመዘገበ ነው ብለዋል፡፡
እየተመዘገቡ ያሉ ለውጦች ኢትዮጵያ በቀጣይ ጥቂት ዓመታት የምትደርስበትን ከፍታ የሚያመላክቱ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡
በሀገሪቱ የተሟላ የኢኮኖሚ ሪፎርም ተግባራዊ መደረጉ በዘርፋ የሚታዩ በተለይም የዋጋ ግሽበትን፣ የውጭ ምንዛሪ መዛባትንና አቅርቦት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ ተግባራት የተከናወኑበት ነው።
በዚህም ለእመርታችን መሠረት የሆኑ መልካም ውጤቶችን እየተመለከትን ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!