ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኅብረት ም/ፕሬዚዳንት ጋር መከሩ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኅብረት ምክትል ፕሬዚዳንት ቴሬሳ ሪቤራ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ከ2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ ጎን ለጎን ከአውሮፓ ኅብረት ም/ፕሬዚዳንት ቴሬሳ ሪቤራ ጋር ተወያይተናል ብለዋል፡፡
በውይይታቸውም በተለያዩ የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ነው የገለጹት፡፡