Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራና በታዳሽ ሃይል ያስመዘገበችው ውጤት አርአያ የሚሆን ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2017 (ኤፍ ኤምሲ) ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ እና በታዳሽ ሃይል ያስመዘገበችው ውጤት ለሁላችንም አርአያ የሚሆን እና የሚያነሳሳ ነው አሉ የ2025 ኮፕ ሊቀ መንበር አምባሳደር አንድሬ ኮሬያ ዴ ሎጎ።

ብራዚል የ30ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ኮንፈረንስ (ኮፕ 30) ሊቀ መንበር ስትሆን÷ መድረኩን ለማስተናገድም እየተሰናዳች ትገኛለች፡፡

አምባሳደር አንድሬ ኮሬያ ዴ ሎጎ በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ ላይ እንዳሉት÷ አፍሪካ እና ብራዚል ዘመናትን የተሻገረ ታሪካዊና ጥብቅ ትስስር አላቸው፡፡

የአፍሪካውያን ሕብረት ለዓለም ትልቅ ስጦታ መሆኑን ገልጸው÷ የአፍሪካውያንን ድምጽ የተቀረው ዓለም በአጽንኦት ሊገነዘብ ይገባል ብለዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ ያልተገመተ ተፅዕኖና ቀጣናዊ ተግዳሮቶች ጋር ተዳምሮ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመዋጋት፣ ብራዚል በኮፕ ሊቀመንበርነቷ ሶስት ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል።

እነዚህም ዓለም አቀፋዊ ብዝሃነትና የአየር ንብረት ለውጥ በጋራ እንዲቆሙ ማስቻል፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተግባራት ከሰው ልጆች ሕይወት ጋር በቀጥታ እንዲገናኙ ማስቻልና የፓሪስ ስምምነት ተግባራዊነት እንዲፋጠን መስራት ናቸው፡፡

ኮፕ 30 የዓለም አቀፋዊ ብዝሃነት ተሳትፎ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እንዲተባበር የማድረግ ግብ እንዳለውም አስረድተዋል፡፡

ዓለም የአየር ንብረት ለውጥን ለአፍሪካ ጭምር መዋጋት እንዳለበት እና አህጉሪቱ ለአየር ንብረት ለውጥ ያላት ድርሻ በጣም አነስተኛ መሆኑን ጠቅሰው÷ ይህም ፍትሃዊ አይደለም ነው ያሉት።

የአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካንና ሌሎች ሀገራትን ምጣኔ ሃብትና ሕልውና የሚፈታተን በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኝ በመትከል ያስመዘገበች ስኬት እንዲሁም በታዳሽ ሃይል ላይ እያከናወነች የምትገኘው የማይበገር የሃይል አማራጭ የመፍጠር ሒደት አርአያ የሚሆንና የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።

ብራዚል በኮፕ 30 ሊቀመንበርነቷ የአፍሪካን አንገብጋቢ እና ዓበይት አጀንዳዎች በመደገፍ ተገቢ ድጋፍ እንዲያገኙ ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል፡፡

በመሳፍንት ብርሌ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.