Fana: At a Speed of Life!

የሕዳሴ ግድብ የጥቁር ሕዝቦች ሁሉ ታሪክ ሆኖ የሚኖር ታላቅ ገድል ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2017 (ኤፍ ኤምሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የጥቁር ሕዝቦች ሁሉ ታሪክ ሆኖ የሚኖር ታላቅ ገድል ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

ኢትዮጵያውያን የዘመናት ቁጭት የነበረው ታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ የምረቃ ሥነ ሥርዓት በጉባ እየተካሄደ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ የሕዳሴ ግድብ የትናትን ቁጭት ማሰሪያ የመጪው ንጋት ማብሰሪያ ነው ብለዋል፡፡

ቀድም ሲል ዓባይ እግር እንጂ አፍ ስላነበረው ብዙዎች ሲናገሩለት ቆይታዋል፤ በዛሬው ዕለት ግን አፍ አውጥቶ መናገር ጀምሯል ነው ያሉት፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአካል ሄዶ መጎብኘት እንዳለበት ጠቁመው÷ በቦታው ተገኝቶ መመልከት ልዩ ትርጉም እንዳለው አውስተዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት ንጋት ሐይቅ 74 ትሪሊየን ሊትር ውሃ መያዝ ችሏል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ይህም በአንድ ብር ቢታሰብ 74 ትሪሊየን ብር ማለት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.