Fana: At a Speed of Life!

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሕዳሴ ግድብ በመመረቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለምረቃ በመብቃቱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ያስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
ኢትዮጵያ የሚለው ስም ጽርዓዊ፣ ደኃራዊ ስም ሲሆን ቀደም ሲል የኖኅ የልጅ ልጅ በሆነው በኵሽ ምክንያት የኵሽ ምድር እንዲሁም ምድረ አዜብ፣ ምድረ ሳባ፣ ምድር ኣግዐዚት በመባል ተጠርታለች፡፡
ለዘመናት ኢትዮጵያን ቋሚ አድርገው ካቆዩ ዐምዶች መካከልም ፈለገ ግዮን የተባለው የዓባይ ወንዝ እና ‹‹ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች››
በመሆኑም በመግቢያችን ላይ ባነሳነው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የኢትዮጵያ ትእምርት ተደርጎ የተጠቀሰው ፈለገ ግዮን በእኛ ዘመን ለሕዝቡ ብርሃን እያበራ አገልግሎት መስጠት የሚችልበት ሁኔታ ተፈጥሮ በማየታችን ከሁሉ አስቀድመን ለእግዚአብሔር አምላካችን ምስጋና እናቀርባለን፡፡
በማስከተልም የዛሬዋን ቀን በመናፈቅ የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ዕለት አንስቶ አቅማችሁ የፈቀደውን ሁሉ ለዚህ ሥራ በማዋጣት ታሪክ በመልካም የሚያስታውሰውን ዋጋ የከፈላችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ልጆቻችንን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡
በመጨረሻም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ወደቀጣይ የልማት ሥራ የሚያሸጋግር እንዲሆን፣ ከምንም በላይ ሰላም በምድራችን ላይ እንዲሰፍን ሕዝባችንም እግዚአብሔር የሰጠውን በነፃነት የመኖር መብት ተከብሮለት የልማቱን በረክት መሳተፍ እንዲችል ሁሉም ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ስንል አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.