Fana: At a Speed of Life!

10ኛው የከተሞች ፎረም በሰመራ ሎጊያ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 10ኛው የከተሞች ፎረም በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ፎረሙ “የከተሞች ዕድገት ለኢትዮጵያ ልሕቀት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ከሕዳር 6 እስከ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በሚካሄደው ፎረም ላይ ከ150 በላይ ከተሞች፣ ከ10 በላይ የንግድ ድርጅቶች እና ከጎረቤት ሀገራት የተወጣጡ ከተሞች ተሳትፈዋል፡፡

በቤዛዊት ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.