በሕዳሴ ግድብ የዘመናት ምኞት በዘመናችን ተሳካ፤ የኢትዮጵያ ማንሠራራትም እውን ሆኗል- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ ለምረቃ በመብቃቱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
እነሆ ታሪክ ሲቀየር፣ ዓባይ ሲከተር፣ ትርክት ሲለወጥ፣ ሀብት ሲገለጥ አየን፤ የዘመናት ምኞት በዘመናችን ተሳካ፤ የኢትዮጵያ ማንሠራራትም እውን ሆኗል ነው ያሉት፡፡
ከዚህ በላይ ከፍታ እና ሥራ ይጠብቀናል፤ እኛም ተዘጋጅተናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡