Fana: At a Speed of Life!

የዲጂታላይዜሸን ሥራዎችን በማሳለጥ ነገን የዋጀ አሠራር እናጠናክራለን – እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በየመስኩ የጀመርናቸዉን የዲጂታላይዜሸን ሥራዎችን በማሳለጥ ነገን የዋጀ አሠራርና አደረጃጀት እናጠናክራለን አሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)።

ርዕሰ መስተዳደሩ ‘ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ’ በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት እየተከበረ ያለውን የነገው ቀንን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት፤ ዓለም ዲጂታላይዝድ እየሆነ፣ ዉድድሩም እያየለ መጥቷል።

ዓለማዊ ሁኔታው ተለዋዋጭና ተገማች ወደ ማይሆንበት አውድ መሸጋገሩን ጠቅሰዋል።

በሁሉም ዘርፎች አሠራሮችን ማዘመን፣ ዲጂታላይዝ ማድረግ፣ አገልግሎቶችን ለማቀላጠፍ፣ ምርታማነትን፣ ተወዳዳሪነትንና ውጤታማነትን ከፍ ለማድረግ መሠረታዊ ቅድመ ሁኔታ መሆኑንም አንስተዋል።

ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠል ከዚህ አውድ ጋር ተቀራራቢና ተመጋጋቢ የሆነ ሁሉን አቀፍ ዝግጅትና ተግባር ማጠናከር እጅግ አስፈላጊ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

በየመስኩ የተጀመሩ የዲጂታላይዜሸን ሥራዎችን በማሳለጥ ነገን የዋጀ አሠራርና አደረጃጀት እንደሚጠናከር ገልጸው፤ በዚህም የመልካም አስተዳደርና የልማት ግንባታችንን ከፍ በማድረግ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እንተጋለን ብለዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.