20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ በቶኪዮ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በነገው ዕለት በጃፓን ቶኪዮ ከተማ በይፋ ይጀመራል፡
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከ800 ሜትር ጀምሮ እስከ ማራቶን ባሉ ርቀቶች እንዲሁም በእርምጃ ውድድር በሁለቱም ጾታ ትሳተፋለች፡፡
በውድድሩ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም በተለያየ ዙር ወደ ጃፓን ቶኪዮ ከተማ አቅንተዋል፡፡
ቀደም ሲል ቶኪዮ የገባው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ በትናንትናው ዕለት የመጀመሪያውን ልምምድ አድርጓል፡፡
ከመስከረም 3 እስከ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በቶኪዮ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ 2 ሺህ በላይ አትሌቶች ይሳተፋሉ፡፡
በሻምፒዮናው በ49 ዘርፎች ውድድር የሚካሄድ ሲሆን ÷147 ሜዳልያዎችም ለአሸናፊ አትሌቶች የሚበረከቱ ይሆናል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!