ኢትዮጵያውያን የሰርከስ አርቲስቶች በአሜሪካ ጎት ታለንት ለ1 ሚሊየን ዶላር አሸናፊነት ይወዳደራሉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2025 የአሜሪካ ጎት ታለንት እየተወዳደሩ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን የሰርከስ አርቲስቶች ቶማስ አለሙ እና ታምራት አያሌው ቲቲ ቦይስ ወደ ፍጻሜ ማለፍ ችለዋል።
ቲቲ ቦይስ ከሌሎች 8 ተወዳዳሪዎች ጋር በመፋለም ነው 4 ተወዳዳሪዎች ብቻ ወዳለፉበት የፍጻሜ ውድድር የተቀላቀሉት፡፡
ኢትዮጵያውያኑ የሰርከስ አርቲስቶች ቲቲ ቦይስ በተመልካች እና በውድድሩ ዳኞች ከፍተኛ አድናቆት ተችሯቸዋል።
በዳኞች በተሰጣቸው አስተያየት ሥራቸው ድንቅ የሆነ ተሰጥኦና በዓመቱ ከታዩ ክስተቶች አንዱ ነው ተብሎላቸዋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰርከስ ማህበር ጥምረት ፕሬዚዳንት ተክሉ ተሻገር ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያውያን በዚህ ዓለም አቀፍ ግዙፍ የተሰጥኦ ውድድር መድረክ ለፍጻሜ ሲደርሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡
ይህም ለኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሁሌም የሚጠቀስ ትልቅ ስኬት መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
የውድድሩ ሽልማት የሆነውን 1 ሚሊየን ዶላር ለማሸነፍ የሕዝብ ድምፅ ወሳኝ ሲሆን ÷ ለተወዳዳሪዎች ድምፅ በመስጠት ልንደግፋቸው ይገባል ሱሉም ጠይቀዋል፡፡
በመለሰ ምትኩ