Fana: At a Speed of Life!

የሕዳሴ ግድብን መጠናቀቅ በማስመልከት በጋምቤላ እና አሶሳ ከተሞች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ ለምረቃ መብቃቱን በማስመልከት በጋምቤላ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

በጋምቤላ በተካሄደው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ወጣቶች ተሳትፈዋል።

ርዕሰ መስተዳድሯ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፥በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የታየውን ስኬት በሌሎች የልማት ስራዎች ለመድገም ጠንክርን ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

‎በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ “በህብረት ችለናል” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የስፖርት ቤተሰቦች ተሳታፊ ሆነዋል።

ግድቡ ለምረቃ መብቃቱን በማስመልከት በክልሉ የተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተካሄዱ ሲሆን፥ በነገው ዕለት የደስታ መግለጫ ሕዝባዊ ሰልፍ መዘጋጀቱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገልጿል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ ባሳለፍነው ማክሰኞ ለምረቃ መብቃቱ የሚታወስ ሲሆን፥ በመላ ሀገሪቱ ህዝቡ ደስታውን በመግለጽ ላይ ይገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.