ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በስፖርት ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በስፖርት ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ ነፊሳ አልማህዲ ከሩሲያ ስፖርት ፌዴሬሽን ሚኒስትር ሚካኤል ዴግትያረቭ ጋር በትብብር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትር ዴዔታዋ በወቅቱ እንዳሉት፤ የረጅም ጊዜ ግንኙነት ያላቸው ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በተለያዩ ዘርፎች በትብብር እየሰሩ ነው።
ይህንን ትብብር በስፖርት ዘርፍም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ በስፖርት ልማት ዘርፍ ስልጠናዎች፣ ስፖርት ሳይንስ፣ ስነ-ምግብና ስፖርት አካዳሚ አስተዳደር እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግር በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።
ሚካኤል ዴግትያረቭ በበኩላቸው ግንኙነታችንን በማጠናከር በስፖርት ዘርፍ በጋራ እንሰራለን ብለዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!