Fana: At a Speed of Life!

የኬንያ ምሁራን ለተፋሰሱ ሀገራት ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስላለው ሕዳሴ ግድብ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኬንያ ምሁራን ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለቀጣናዊ ትስስር እና ለናይል ተፋሰስ ሀገራት ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል አሉ፡፡

በአሜሪካ ዌበር ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ምሁር የሆኑት ጆን ሙኩም ምባኩ ለኬቢሲ ቴሌቪዥን እንዳሉት÷ ግድቡ የናይል ወንዝ 86 በመቶ ድርሻ ያላት ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ችግሯን እንድትፈታ ያስችላል።

የሕዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ እና ለናይል ተፋሰስ ሀገራት የለውጥ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸው÷ ግድቡ ለቀጣናዊ ትስስር እና የጋራ እድገት ወሳኝ እንደሆነ አመላክተዋል።

የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ጆን ራኦ ኒያሮ በበኩላቸው÷ ግድቡን በተመለከተ በፈረንጆቹ 1929 እና 1959 የተደረጉ የቅኝ ግዛት ወቅት ስምምነቶች የናይል ውሃ 86 በመቶ ድርሻ ያላትን ኢትዮጵያ ያገለሉ እንደሆኑ ተናግረዋል።

ስምምነቶቹ በተቀራኒው በወንዙ ላይ ምንም አስተዋጽኦ የሌላቸውን ግብፅ እና ሱዳንን ብቻ ተጠቃሚ ያደረጉ መሆናቸው ተገቢ እንዳልሆነም አስገንዝበዋል።

እነዚህን ጊዜ ያለፈባቸው የቅኝ ግዛት ስምምነቶች ለማሻሻል ሶስቱ ሀገራት በናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ላይ ደርሰው እንደነበር አስታውሰዋል።

የሕዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ያለውን የኤሌክትሪክ ሀይል ችግር ይፈታል ያሉት ጆን ራኦ ኒያሮ÷ በተመሳሳይ ግብፅ እና ሱዳንን ከደለል እና ጎርፍ አደጋ እንደሚጠብቃቸው አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም ግድቡ የተረጋጋ የውሀ ፍሰት እንዲኖር እንደሚያደርግ በመጠቆም፤ በዚህም ሱዳን እና ግብፅ ለመስኖ፣ ለቤት ውስጥ እና ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውል ጤናማ ፍሰት ያለው ውሃ እንዲኖራቸው ያደርጋል ብለዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.