Fana: At a Speed of Life!

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክቶ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተካሄዱ የድጋፍና ደስታ መግለጫ ሰልፎች ላይ የተላለፉ መልዕክቶች፡-

👉 ‎የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ምልክት፤ ‎በትክክለኛ ጊዜ የተገነባ ዘመን ተሻጋሪ ቅርስ ነው፣

👉 ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሕብረ ብሔራዊነታችን እና የአንድነታችን መሠረት ፣ የውጭ ተጽዕኖ ያልበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነት ላይ የቆመ ግድብነው፣

👉 የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ማሳያ ነው፤ ግድቡ የመንግስት ጠንካራ አመራር ሰጪነት እና የሕብር ውጤት ነው፣

👉 ሕዳሴ ግድብ የማይቻለውን ችለን ያሳየንበት ነው፤ በግድቡ ላይ ያሳየነውን አንድነት በሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች ላይ እንደግማለን ፣

👉 ግድባችን በኢትዮጵያዊነት ኅብር ጸንቶ የቆመ የ‎አሸናፊነታችን ኒሻን ነው ፤ በኅብረት ችለናል ጨርሰን አሳይተናል፣

👉 የሕዳሴ ግድብ የትላንት ቁጭት ማሰሪያ የመጭው ንጋት ማብሰሪያ ነው፤ ኢትዮጵያ ትችላለች፣

👉 የሕዳሴ ግድብን ማጠናቀቅ የአሸናፊነት አክሊል መድፋት ነው ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማንነታችን እና ብሔራዊ ዓርማችን ነው፣

👉 ሕዳሴ ግድብ በራሳችን አቅም የገነባነው የአንድነታችንና የአብሮነታችን መገለጫ ነው፤ የሚደገም ድል፤ የሚጨበጥ ብስራት ሕዳሴ ግድብ፣

👉 ‎ሕዳሴ ግድብ የዓባይ ዘመን ትውልድ የተጋድሎ ሰንደቅ ፤ የልፋታችን እና የጠብታችን ማብሰሪያ ነው፣

‎ 👉 ግድባችን የታሪክ ስብራት መጠገኛ ሆኗል ፤ በመተባባር ክንድ የኢትዮጵያ ጉዞ እውን ይሆናል፣

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.