ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክቶ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተካሄዱ የድጋፍና ደስታ መግለጫ ሰልፎች ላይ የተላለፉ መልዕክቶች፡-
👉 የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ምልክት፤ በትክክለኛ ጊዜ የተገነባ ዘመን ተሻጋሪ ቅርስ ነው፣
👉 ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሕብረ ብሔራዊነታችን እና የአንድነታችን መሠረት ፣ የውጭ ተጽዕኖ ያልበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነት ላይ የቆመ ግድብነው፣
👉 የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ማሳያ ነው፤ ግድቡ የመንግስት ጠንካራ አመራር ሰጪነት እና የሕብር ውጤት ነው፣
👉 ሕዳሴ ግድብ የማይቻለውን ችለን ያሳየንበት ነው፤ በግድቡ ላይ ያሳየነውን አንድነት በሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች ላይ እንደግማለን ፣
👉 ግድባችን በኢትዮጵያዊነት ኅብር ጸንቶ የቆመ የአሸናፊነታችን ኒሻን ነው ፤ በኅብረት ችለናል ጨርሰን አሳይተናል፣
👉 የሕዳሴ ግድብ የትላንት ቁጭት ማሰሪያ የመጭው ንጋት ማብሰሪያ ነው፤ ኢትዮጵያ ትችላለች፣
👉 የሕዳሴ ግድብን ማጠናቀቅ የአሸናፊነት አክሊል መድፋት ነው ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማንነታችን እና ብሔራዊ ዓርማችን ነው፣
👉 ሕዳሴ ግድብ በራሳችን አቅም የገነባነው የአንድነታችንና የአብሮነታችን መገለጫ ነው፤ የሚደገም ድል፤ የሚጨበጥ ብስራት ሕዳሴ ግድብ፣
👉 ሕዳሴ ግድብ የዓባይ ዘመን ትውልድ የተጋድሎ ሰንደቅ ፤ የልፋታችን እና የጠብታችን ማብሰሪያ ነው፣
👉 ግድባችን የታሪክ ስብራት መጠገኛ ሆኗል ፤ በመተባባር ክንድ የኢትዮጵያ ጉዞ እውን ይሆናል፣