Fana: At a Speed of Life!

የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የኢትዮጵያን የብልፅግና ስኬት አይቀሬነት ያረጋገጠ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መገንባት የኢትዮጵያን የብልፅግና ስኬት አይቀሬነት ያረጋገጠ ነው አሉ በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዲላ ክላስተር አስተባባሪ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) ።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅን በማስመልከት በዲላ ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፍ ተካሂዷል።

አቶ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር ) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ስኬት የኢትዮጵያ የከፍታና የማንሰራራት ጉዞ ማሳያ ነው።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መገንባት የመቻል አቅም የታየበት እንደሆነ እና ከድህነት አዙሪት በመውጣት የኢትዮጵያን የብልፅግና ስኬት አይቀሬነት ያረጋገጠ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ደስታው የሁላችንም ነው ያሉት ኃላፊው÷ ለዚህ ስኬት በመብቃታችን እንኳን ደስ አለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ ሕዳሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ሕዳሴ ግድብ በሕብረት በመቆም፤ በፅናትና በትጋት ለስኬት እንዲበቃ መደረጉን ተናግረዋል።

የዞኑ ሕዝብ ለግድቡ ግንባታ ሁለንተናዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው÷ በቀጣይ ግዙፍ ሃገራዊ ፕሮጀክቶች እንዲሳኩ ተሳትፎውን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.