Fana: At a Speed of Life!

የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የጀግንነት ታሪክ ዳግም በደማቅ ቀለም የተጻፈበት ነው – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‌‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የድል እና የጀግንነት ታሪክ ዳግም በደማቅ ቀለም የተጻፈበት ነውአሉ።

የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ መመረቁን አስመልክቶ ‘በኅብረት ችለናል’ በሚል መሪ ሀሳብ በቦንጋ ከተማ ክልል አቀፍ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በሰልፉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ግድቡ የጀግንነት ታሪክ የተጻፈበት የዘመናችን የብልጽግና አሻራ ነው ብለዋል።

‎በቅኝ ግዛት ህግ በሀብታችን እንዳንጠቀም ሲሰራብን የቆየ ቢሆንም ይህንን በመስበር የአንድነታችን ማህተም የሆነውን ሕዳሴ ግድብ በላብ እና በደም ጠብታ ዕውን አድርገናል ነው ያሉት።

በአንድነት ስንቆም ከመልማት የሚያግደን የለም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ‎ኢትዮጵያ ግድቡን ዕውን ያደረገችው በኢትዮጵያ ጥቅም የማይደራደሩ መሪና ህዝቦችን በማፍራቷ እንደሆነ ተናግረዋል።

ህብረ ብሔራዊ አንድነትን አጠናክሮ በማስቀጠል ወደፊት ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ዕውን ለማድረግ የሕዳሴ ግድብ መመረቅ ማሳያ መሆኑን አመልክተዋል።

‎የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በበኩላቸው፤ የውጭ እና የውስጥ ፈተናዎችን በማለፍ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ለፍጻሜ ማብቃቷ ትልቅ ድል መሆኑን ገልጸዋል።

የካፋ ዞን ማህበረሰብ ለግድቡ ግንባታ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፤ በሌሎች ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ አንድነታችንን በማጠናከር ድጋፋችንን እናስቀጥላለን ብለዋል።

‎በፍሬው አለማየሁ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.