በመርሲሳይድ ደርቢ ሊቨርፑል ኤቨርተንን 2 ለ 1 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ሊቨርፑል ኤቨርተንን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
በአንፊልድ በተደረገው ጨዋታ ሪያን ግራቨንበርች እና ሁጉ ኢኪቲኬ የሊቨርፑልን ጎሎች ሲያስቆጥሩ የኤቨርተንን ብቸኛ ጎል ኤዲሪሳ ጉየ አስቆጥሯል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም ሊቨርፑል ነጥቡን ወደ 15 ከፍ በማድረግ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡