ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ከ5ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ ጎን ለጎን ባደረግነው ውይይት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራና ለዘመናት የቆየ ግንኙነት በድጋሚ አረጋግጠናል ብለዋል፡፡
ተግባራዊ ትብብርንና ተጨባጭ ውጤቶችን በማምጣት አጋርነታችንን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረናል ነው ያሉት፡፡