Fana: At a Speed of Life!

ሕዳሴ ግድብ የመደመር ዕሳቤ የታተመበት ፕሮጀክት ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዳሴ ግድብ ከጫፍ እስከ ጫፍ በሁሉም የኢትዮጵያ ማዕዘናት የኢትዮጵያ ልጆችን ለልማት ያስተባበረና የመደመር ዕሳቤ የታተመበት ፕሮጀክት ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ተራሮች በሸለቆ እና በሜዳ ገሰግሶ እንደሚገናኘው ታላቁ ዓባይ የብዝሃነት ቤት በሆነችው ድሬዳዋ የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ ዛሬ የድጋፍ ሰልፍ ተደርጓል ብለዋል።
በሕዳሴ ግድብ ያየናቸው በፈተናዎች መካከል እንደ አለት ጸንቶ በመቆም ማሸነፍ በድሬዳዋ ያሉ የልማት አቅሞችን ለሀገር ልማት ለማዋል ብርታት ይፈጥራል ነው ያሉት።
ድሬዳዋ የሰላም እና የፍቅር ብቻ ሳይሆን ለልማት እና ለውጥ መበርታትም መገለጫዋ ነው ሲሉም አመልክተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.