Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ መካከል የሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ ቀጥሎ መካሄድ ጀምሯል

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ መካከል በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ ቀጥሎ መካሄድ ጀምሯል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሚካሄደው የጋራ ስብሰባ በአፍሪካ ሕብረት አስተባባሪነት ዛሬ ከስዓት በኋላ በበይነ መረብ መካሄድ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

የዛሬው ስብሰባ በአፍሪካ ሕብረት አስተባባሪነት እየተካሄደ የሚገኘው የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በስብሰባው የአፍሪካ ሕብረት ቢሮ ታዛቢዎች፣ የአፍሪካ ሕብረት ባለሙያዎች የአውሮፓ ሕብረት እና የአሜሪካ ታዛቢዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.