Fana: At a Speed of Life!

በ24 ሰዓታት 982 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ19 ሰዎች ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 19 ሺህ 769 የላብራቶሪ ምርመራ 982 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 29 ሺህ 876 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።

ከዚህ ባለፈ የ19 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 528 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 322 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 12 ሺህ 359 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን 609 ሺህ 463 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 29 ሺህ 786 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 16 ሺህ 687 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 217 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 12 ሺህ 359 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ528 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.