የበዓል ወቅት አመጋገብ ጥንቃቄ…
አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የበዓላት ወቅት አመጋገብ ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገበት ለጤና ችግር ሊዳርግ እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
በመሆኑም የበዓላት ወቅት አመጋገብን ጥንቃቄ የተሞላበት ማድረግ እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡
ምክንያቱም ቅባት የበዛበት ምግብ መመገብ ጨጓራን ለህመም የመዳረግ ዕድሉ ከፍተኛ ስለሚሆን ነው፡፡
ጥንቃቄ የጎደለው አመጋገብ ከሆነ÷ እንደ ሆድ መንፋት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጨጓራ ማቃጠል እና ሌሎች ህመሞችንም ሊያስከትል እንደሚችል ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
በመሆኑም በዓላትን የጤና መታወክ ሳያጋጥም ለማሳለፍ÷ የሚዘጋጀው ምግብ ንጽህናው እንዲጠበቅ እንዲሁም ምግቦች ቅባት የበዛባቸው እንዳይሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
በአመጋገብ ወቅትም ቀስ በቀስ ጨጓራን በማላመድ መሆን እንዳለበት ይመከራል።
ጣፋጭ ምግቦችን እና የአልኮል መጠጦችን ከልክ በላይ ባለመውሰድ እራስን እና ቤተሰብን ከህመም መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎች ያስገነዝባሉ።