Fana: At a Speed of Life!

መንግሥት በየደረጃው የሚታዩ የአገልግሎት ጉድለቶችን ለማረም እየሠራ ነው – ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግሥት በየደረጃው የሚታዩ የአገልግሎት ጉድለቶችን ለማረም እየሠራ ነው አሉ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)።

በአማራ ክልል ባሕር ዳር ከተማ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በዛሬው ዕለት ሥራ ጀምሯል።

ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰው ተኮር የአገልግሎት ልህቀትን የሚያረጋገጥ ነው።

የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በመፍታት ወደ ልህቀት የሚያሸጋግሩ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶች እየሰፉ መሆኑን አንስተው፥ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ከፌዴራል ጀምሮ በክልሎች እየሰፋ ይገኛል ብለዋል።

የአገልግሎት አሰጣጥ ችግርን ለመፍታት እንደ ሀገር እየተሠራ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በመሶብ ዜጎች የሚፈልጉትን አገልግሎት በአንድ ማዕከል የሚያገኙበት እንደሆነ ጠቅሰው፥ ይህም መንግሥት እና ሕዝብን የሚያቀራርብ እንደሆነ አብራርተዋል።

የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ተጨባጭ ውጤቶች እያሳዩ እንደሆነ እና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች የውጤቶቹ ማሳያ መሆናቸውን በማንሳት የፌዴራል መንግሥት የሚጠበቅበትን ድጋፍ ያደርጋል ነው ያሉት።

ማዕከሉን የተስፋ ማዕከል አድርጎ መመልከት እና መጠበቅ እንደሚገባ እንዲሁም አገልግሎቱን በሌሎች ከተሞችም ማስፋት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ባንቺዓምላክ ገብረ ማርያም በበኩላቸው፥ የአግልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመሻገር የተለያዩ ተግባራት እየተሠሩ መሆናቸውን መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.